በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ "ከመሸመት ወደ ማምረት" በሚል መሪ ሐሳብ የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ እየተካሄደ ይገኛል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ኤክስፖውን በከፈቱበት ወቅት እንደገለጹት፣ በክልሉ መካሄድ የጀመረው የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ኢትዮጵያ በየአቅጣጫው ያሏት የኢንዱስትሪ አቅሞች በመደመር ብልፅግናዋን ዕውን ማድረግ የሚያስችል ነው።
በክልሉ የሚገኙ የተፈጥሮ ሀብቶችን ወደ ተጨባጭ ሀብት በመቀየር አርሶአደሮች የማምረት አቅማቸውን ማሳደግ አለባቸው ያሉት አቶ አሻድሊ፣ በክልሉ ኢንዱስትሪዎች ቁጥር እና የማምረት አቅማቸውን እንዲያሳድጉ የክልሉ መንግስት ከፍተኛ ትኩረት እንደሚሰጥ አንስተዋል።
የክልሉ መንግሥት ለባለሀብቶች ምቹ ሁኔታን በመፍጠር የኢንዱስትሪ እና የኢንቨስትመንት ዘርፉ እንዲስፋፋ በቅርበት እንደሚደግፍ ገልጸዋል።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ አመንቴ ገሺ በበኩላቸው፣ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የሀገር ውስጥ ምርትን ለመጨመር እና የአምራቹንና የሸማቹ ግንኙነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚያግዝ መሆኑን ተናግረዋል።
የክልሉ መንግሥት ኢንዱስትሪውን በሚፈለገው ልክ ለውጥ እንዲያመጣ እንዲሁም ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅማቸውን እንዲያሳድጉ የመሠረተ ልማት ሁኔታዎች ማመቻቸት አስፈላጊ ነው ተብሏል።
በኤክስፖው አምራቾች የተለያዩ ምርቶችን ያቀረቡ ሲሆን፣ እስከ ጳጉሜ 1 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚቆይ ተገልጿል።
በነስረዲን ሐሚድ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: