ለኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ጸሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ በሃይማኖት ተቋማት ለሰላም ላበረከቱት አስተዋፅኦ ዓለም አቀፍ እውቅና ተሰጥቷቸዋል።
እውቅናውን የሰጠው 56 ሀገራትን በአባልነት ያቀፈው ዓለም አቀፍ ፒስ ሜከርስ ኔትዎርክ አድቫይዘሪ ግሩፕ የ2026 ስብሰባን በአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን አዳራሽ ባካሄደበት ወቅት ነው።
የሃይማኖት እና የማኅበረሰብ መሪዎች በግጭት አፈታት እና በዘላቂ ሰላም ግንባታ የላቀ አበርክቶ እንዳላቸው የተገለጸ ሲሆን፣ ቀሲስ ታጋይ ታደለ በኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ውስጥ ለዘላቂ ሰላም ግንባታ ሰፊ አስተዋፅኦ ማበርከታቸው እውቅና እንዲሰጣቸው ማድረጉ በመድረኩ ላይ ተነስቷል።
በመድረኩ የተገኙት የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን የመደመር መንግሥት ሰፊ ሥራ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸው፣ በቅርቡ ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደው ሀገራዊ ምክክር ለዚህ ማሳያ ነው ብለዋል።
በመርሐ ግብሩ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ተወካዮች፣ አምባሳደሮች፣ የተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቶች እና የሰላም ፎረም ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።
በመሐመድ ራህመቶ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: