Search

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን ገለጹ

ቅዳሜ መስከረም 02, 2019 184

 

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በኢትዮጵያ እና ሩሲያ መካከል ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) እንደገለጹት፣ ውይይቱ በመከላከያ እና ደኅንነት፣ በንግድ እና ኢንቨስትመንት፣ በትምህርት እንዲሁም በቴክኖሎጂ መስኮች ያለውን ትብብር ለማሳደግ ያለውን የጋራ ቁርጠኝነት በድጋሚ የተረጋገጠበት ነው።

በተጨማሪም የትምህርት ልምድ ልውውጦችን ማስፋት፣ በባህል እና በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ላይ ያለውን ትብብር ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ዕድሎች ዙሪያ መምከራቸውን አብራርተዋል።

በሌላ በኩል፣ ለኮፕ 32 በሚደረገው ዝግጅት ያለውን አጋርነት ጨምሮ፣ በአየር ንብረት ለውጥ እና በልማት ግቦች ዙሪያ ትብብሮችን ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታዎች ላይ ውይይት መደረጉን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

 

በመጨረሻም በወል ተጠቃሚነት ላይ የተመሠረቱ የንግድ እና የኢኮኖሚ ልውውጦችን ይበልጥ ለማስፋፋት በጋራ ለመሥራት መስማማታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) አረጋግጠዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: