Search

18ኛው የብሪክስ መሪዎች ጉባኤ በሕንድ ኒው ዴልሂ መካሄድ ጀመረ

ቅዳሜ መስከረም 02, 2019 32
ለሁለት ቀናት የሚቆየው 18ኛው የብሪክስ መሪዎች ጉባኤ በሕንድ ኒው ዴልሂ “ጽናትን፣ ፈጠራን፣ ትብብርን እና ዘላቂነትን መገንባት” በሚል መሪ ቃል መካሄድ ጀምሯል።
በጉባኤው ላይ የብሪክስ አባል እና አጋር ሀገራት መሪዎች እና የዓለም አቀፍ ተቋማት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የሚሳተፉ ሲሆን፣ የብሪክስ አባል ሀገር የሆነችው ኢትዮጵያም በጉባኤው ላይ ተሳትፎ እያደረገች ትገኛለች።
በጉባኤው ላይ ለመሳተፍ ኒው ዴልሂ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከጉባኤው ጎን ለጎን ከተለያዩ ሀገራት መሪዎች ጋር ተወያይተዋል።
መሪዎቹ በዓለም አቀፍ ደረጃ እያደገ የመጣውን የዲፕሎማሲ እና የኢኮኖሚ ትብብርን ይበልጥ ማጠናከር በሚያስችሉ አጀንዳዎች ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
 
 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: