Search

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሂም ጋር ተወያዩ

ቅዳሜ መስከረም 02, 2019 51
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከብሪክስ ጉባኤ ጎን ለጎን ከማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሂም ጋር ተገናኝተው መምከራቸውን አስታውቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ‎በሕዳር 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ካደረጉት ታሪካዊ ጉብኝት የተገኘውን መልካም ዕድል ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተናል ብለዋል።
‎ውይይታቸውም ኢንቨስትመንትን፣ ቱሪዝምን፣ የታዳሽ ኃይል አጋርነትን ማስፋፋት እና ወደ ኮፕ 32 በሚደረገው ጉዞ ላይ ያለንን ትብብር ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑን ገልጸዋል።
በተጨማሪም በማሌዢያ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት፣ ምርታማነት እና የአምራች ዘርፍ ተሞክሮዎችን መውሰድ በሚቻልባቸው ዕድሎች ዙሪያ መክረናልም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።
‎ኢትዮጵያና ማሌዢያ ጠንካራ የኢኮኖሚ አጋርነት ለመመስረት የሚያስችል ከፍተኛ አቅም አላቸው፤ ይህም በኢንቨስትመንት፣ በቴክኖሎጂ፣ በክህሎት እና በዘላቂ ልማት ማዕቀፎች አዳዲስ ዕድሎችን የሚፈጥር ነው ብለዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: