ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከብሪክስ ጉባኤ ጎን ለጎን ከኢራኑ ፕሬዚዳንት መስዑድ ፔዜሽኪያን ጋር ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፣ በብሪክስ ፕላስ የቤተሰብ መድረክ ማዕቀፍ ውስጥ፣ ከኢራኑ ፕሬዚዳንት መስዑድ ፔዜሽኪያን ጋር ተወያይተናል ብለዋል።
ከጉባኤው ጎን ለጎን ያደረጉት ውይይት በቀይ ባሕር አካባቢ ባሉ ወቅታዊ ሁነቶች እና አጠቃላይ በቀጣናው የደኅንነት ሁኔታ ላይ ያተኮረ መሆኑን አመልክተዋል።
የውይይትን አስፈላጊነት እና የቀጣናውን መረጋጋት እውን ማድረግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያም መምከራቸውን ገልጸዋል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: