Search

የውጭ ሀገራት ኤምባሲዎች ለኢሬቻ በዓል የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላለፉ

ቅዳሜ መስከረም 23, 2019 80

በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ በድምቀት፣ በደስታና በወንድማማችነት ስሜት የሚከበረውን የኢሬቻ በዓል ምክንያት በማድረግ በመዲናችን አዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት ኤምባሲዎች ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ልባዊ የመልካም ምኞትና የደስታ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በዚህም መሰረት የጀርመን፣ የአሜሪካ፣ የብሪታንያ፣ የህንድ፣ የስዊድን፣ የፈረንሳይ እና የሌሎችም ሀገራት ኤምባሲዎች ለኢትዮጵያውያን ደስታ ይፋዊ የመልካም ምኞት መልዕክታቸውን በማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻቸው አጋርተዋል።

ኤምባሲዎቹ በመልዕክታቸውም በዓሉ የሰላም፣ የአንድነት እንዲሁም የደስታና የአዲስ ተስፋ ብስራት ይዞ እንዲመጣ ምኞታቸውን ገልጸዋል።

ዓለም አቀፉ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ ለኢትዮጵያ ባህላዊና ታሪካዊ እሴቶች ያለውን አክብሮት ባሳየበት በዚህ የደስታ አጋጣሚ፣ በዓሉ የፍቅር፣ የይቅርታና የሕብረት ማሳያ ሆኖ በሆራ ፊንፊኔ የተከብበረ ሲሆን በሆራ አርሰዴ ደግሞ ነገ በድምቀት ይከበራል።

በሃና ምንዳሁን

#ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ #ታላቅ_ርዕይ

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: