Search

ከደመና በላይ የCOP32 ጉባኤን ስኬት ለማብሰር ሁሌም ዝግጁ ሆኖ የሚጠብቀው የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ዓርብ ጥቅምት 27, 2019 126

ማንኛውም ታላቅ ጉዞ የሚጀምረው በእምነትና በተቋማዊ ጥንካሬ ነው፤ እያንዳንዱ መዳረሻ ደግሞ ሕዝቦችን፣ ባህሎችንና አዳዲስ ዕድሎችን እርስ በእርስ የሚያስተሳስር ወሳኝ ድልድይ ይፈጥራል።

የአፍሪካ ግዙፉና መሪው የኢትዮጵያ አየር መንገድ (Ethiopian Airlines) የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ብቻ አይደለም፤ ይልቁንም የሀገራችንን ታሪክ፣ ቅርሶች፣ ራዕይና የከፍታ ምኞት ወደ ተለያዩ የዓለማችን ማዕዘናት የሚያደርስ የኢትዮጵያ አምባሳደርና የብሔራዊ ማንነታችን ሕያው መገለጫ ነው።

አየር መንገዱ መዳረሻዎችን ከማያያዝ ባሻገር መላውን ዓለም ከኢትዮጵያ ጋር ያስተሳስራል። የሰው ዘር መገኛ፣ የጽናት ምሳሌና ወደ ተስፋዋ የወደፊት ምዕራፍ በራስ መተማመን የምትራመደውን ሀገራችንን ለዓለም አስተዋውቋል።

አሁን ደግሞ ኢትዮጵያ የምታዘጋጀውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (COP32 Ethiopia) ለማስተናገድ በሚደረገው ሀገራዊ ዝግጁነት ውስጥ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቁልፍ ድርሻውን እየተወጣ ይገኛል።

ዓለም አቀፍ እንግዶችን፣ የሀገር መሪዎችንና የተባበሩት መንግሥታት ልዑካንን በብቃት አስተናግዶ ወደ መዲናችን አዲስ አበባ በማጓጓዝ ረገድ አየር መንገዱ የዝግጅቱ ዋና የትራንስፖርትና የሎጂስቲክስ አምባሳደር ሆኖ ይሰራል።

ይህ ታሪካዊ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ መድረክ የኢትዮጵያን አረንጓዴ ልማትና የአየር ንብረት ለውጥን የመቋቋም አቅም ለዓለም የምናሳይበት ነው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድም የዚሁ አረንጓዴና ዘላቂ የልማት መስመር አካል በመሆን ሀገራዊ ብልጽግናችንን ከደመና በላይ ከፍ አድርጎ ያበስራል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሀገርን ኩራት ተሸክሞ፣ የአህጉርን ተስፋ አስተስስሮ ኢትዮጵያን ወደ ዓለም ያበራል።

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: