ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሩዋንዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ንሰንጊዩምቫ የሁለቱን ሀገራት ትብብር ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን አስታወቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው እንዳመለከቱት፣ በውይይታቸው በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ተግባራዊ ትብብር ማሳደግ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ሰፊ የሀሳብ ልውውጥ አድርገዋል።
ሁለቱ ሀገራት የጋራ ጥቅም ባላቸው የተለያዩ ዘርፎች ላይ ያላቸውን አጋርነት እና ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችሉ ዕድሎችን በተመለከተ መምከራቸውንም ገልጸዋል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: