የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከ30 ሺህ በላይ ተሳታፊዎችን ያሳተፈውን 5ኛውን ዓለም አቀፍ የአፍሪካ የሕዝብ ጤና ጉባኤ (CPHIA 2026) አዲስ አበባ በስኬት እያስተናገደች እንደምትገኝ ገልጸዋል።
ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው፣ አዲስ አበባ፤ የአፍሪካ እና የዓለም አቀፍ ሁነቶች መዳረሻ! በሚል ባስተላለፉት መልዕክት፣ ይህ ታላቅ ጉባኤ የከተማችንን ዓለም አቀፍ ጉባኤዎችን የማስተናገድ አቅም፣ የአገልግሎት ጥራትና የእንግዳ ተቀባይነት ባህል ዳግም ያረጋገጠ ትልቅ ዕድል ነው ብለዋል።
የከተማዋ ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች፣ የቱሪዝም መዳረሻዎች፣ የትራንስፖርትና ሌሎች የአገልግሎት ዘርፎች የኢትዮጵያን ባህል፣ ወግና የእንግዳ አክባሪነት በማሳየት ለከተማዋ ኢኮኖሚያዊ ጥቅምና ዓለም አቀፍ ገጽታ አስተዋጽኦ እያደረጉ እንደሚገኙም አመላክተዋል።
አዲስ አበባ እየተለወጠች ብቻ ሳይሆን፣ የአፍሪካንና የዓለምን ታላላቅ ሁነቶች በስኬት የምታስተናግድ የአህጉሪቱ ዓለም አቀፍ መድረክ እየሆነች ነው ሲሉም አስገንዝበዋል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: