በድንገተኛ ሕመም ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው ተወዳጁ ድምፃዊ ሚኪያስ ቸርነት ሥርዓተ ቀብር በዛሬው ዕለት በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል።
ድምፃዊው በወልቂጤ ከተማ የሙዚቃ ሥራውን እያቀረበ በነበረበት ወቅት ባጋጠመው ድንገተኛ ሕመም ሕይወቱ ማለፉን ይታወሳል።
ሚኪያስ ቸርነት “የኔ ደሃ፣ አሁን ገባኝ፣ ዞዜ፣ ግርማ ሞገሴ ነሽ እና ኪያዬ” በተሰኙ ዜማዎቹ በበርካታ የሙዚቃ አድማጮች ዘንድ ተወዳጅነትን አትርፏል።
ድምፃዊው “ሰላም አላት እና 10 ከ 10 ይገባሻል” የተሰኙ ሁለት አልበሞችን ጨምሮ በርካታ ተወዳጅ ነጠላ ዜማዎችንም ለሙዚቃ አድማጮች አቅርቧል።
ድምፃዊ ሚኪያስ ቸርነት ባለትዳርና የ2 ወንድ እና የ2 ሴት ልጆች አባት ነበር።
ድምፃዊ ሚኪያስ ቸርነት በተወለደ በ45 ዓመቱ ኅዳር 12 ቀን 2019 ዓ.ም ነው ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው።
በሚሊዮን አደም
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: