በመጀመሪያው የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ጉብኝታቸው ያዩት ነገር አሳዛኝ እና ከተነገረው የታቀረነ አንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ።
"የኩስመና ታሪክ ማብቂያ" በሚል ርዕስ ባደረጉት የጉባ ላይ ወግ ቆይታ፣ መጀመሪያ ግድቡን ሲጎበኙ ስለተሰማቸው የተጠየቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ በአካባቢው ሲደርሱ ያዩት ሁኔታ ውል የሌለው ስለነበረ ተበሳጭተው እና ተቆጥተው እንደተመለሱ አስታውሰዋል።
ያኔ የነበረው ሁኔታ አሁን ካለው ሁኔታ ጋር ሲነጻጸር የሰማይ እና የምድር ያክል የተራራቀ እንደነበር ገልፀዋል፡፡
አሁን ያለው ለውጥ ግን የኢትዮጵያን ሕዝብ ፅናት እና በቁርጠኝነት ከተነሱ የማይለውጥ ነገር እንደሌለ ማሳያ እንደሆነ ተናግረዋል።
ግድቡ በርካታ ውስብስብ ነገሮችን አልፎ ለዚህ በመብቃቱ ልዩ ደስታ እንደተሰማቸው ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በመሰናሰልና በመደመር ውስጥ ሆነን ከሰራን አስደናቂ ውጤት ማስመዝገብ እንደምንችል ትምህርት የወሰድንበት ነው ብለዋል፡፡
በለሚ ታደሰ
#PMOEthiopia #AbiyAhmed #EBC #ebcdotstream #GERD #naturalgift