Search

የምድብ ዘጠኝ ተጠባቂ ጨዋታዎች፤ ፈረንሳይ ከ ኢራቅ እና ኖርዌይ ከ ሴኔጋል

ሰኞ ሰኔ 15, 2018 55

በ23ኛው የዓለም ዋንጫ የምድብ ዘጠኝ ተሳታፊ ሀገራት የምድብ ጨዋታቸውን ዛሬ ሲቀጥሉ፤ ፈረንሳይ ከ ኢራቅ እንዲሁም ኖርዌይ ከ ሴኔጋል ይጫወታሉ።

የሁለት ጊዜ የዓለም ሻምፒዮኗ ፈረንሳይ፣ በክዋክብት የተገነባው ስብስቧን እና በፈጣን ሽግግር ላይ የተመሰረተ የማጥቃት እንቅስቃሴዋን በመጠቀም የዛሬውን ጨዋታ በበላይነት ለማጠናቀቅ ወደ ሜዳ ትገባለች።

ይህ ጨዋታ ሌሊት 6:00 ሰዓት ላይ የሚጀምር ሲሆን፣ ፈረንሳይ የዛሬውን ጨዋታ ማሸነፍ ከቻለች በቀጥታ ወደ ቀጣይ ዙር ማለፏን ታረጋግጣለች።

ኢራቆች በምድቡ የመጀመሪያ ጨዋታ በኖርዌይ ከደረሰባቸው የ 4 ለ 1 ሽንፈት በኋላ የመጀመሪያ ሦስት ነጥባቸውን ለማሳካት ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ሌላኛው ተጠባቂ መርሃ ግብር ሌሊት 9:00 ሰዓት ላይ የሚደረገው የኖርዌይ እና የሴኔጋል ጨዋታ ነው።

የአጥቂ መስመሯ በኧርሊንግ ሀላንድ የሚመራው ኖርዌይ፣ ከአፍሪካዋ ተወካይ ሴኔጋል ሊገጥማት የሚችለውን ብርቱ ፉክክር ተቋቁማ በጨዋታው ሦስት ነጥብ በማሳካት ወደ ጥሎ ማለፉ ለመሻገር ጨዋታዋን ታከናውናለች።

May be an image of football, soccer and text

“የቴራንጋ አንበሶች” በሚል ቅጽል ስም የሚታወቁትና ጥንካሬያቸውን በተለያዩ መድረኮች ያስመሰከሩት ሴኔጋሎች፤ በመጀመሪያ የምድብ ጨዋታቸው በፈረንሳይ ከደረሰባቸው የ 3 ለ1 ሽንፈት በኋላ ወደ ድል ለመመለስ ይጫወታሉ።

ሴኔጋሎች በፍጥነታቸው እና በተሳካ የታክቲክ አተገባበራቸው በጨዋታው ለአውሮፓዊቷ ሀገር ኖርዌይ ፈታኝ እንደሚሆኑባት ይጠበቃል።

በዘረንቶስ ሰለሞን