Search

በሰሜን ሸዋ ዞን በሺህዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀብለዋል

ሰኞ ሰኔ 15, 2018 79

መንግሥት ለታጠቁ ኀይሎች በተደጋጋሚ የሰላም አማራጮችን ሲያቀርብ መቆየቱን ተከትሎ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ብቻ 3 ሺህ 162 የታጠቁ ኀይሎች የሰላምን አማራጭ ተቀብለው ትጥቃቸውን መፍታታቸውን ዞኑ አስታውቋል።

No photo description available.

May be an image of one or more people and people smiling

No photo description available.

የሰሜን ሸዋ ዞን ሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ኀላፊ ይደሰቱ ክፈተው እንደገለፁት በ2018 በጀት ዓመት ብቻ ይህ መረጃ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በሺህዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎች በዞኑ የሰላም አማራጭን ተቀብለዋል።

እነዚህም ከተሀድሶ ኮሚሽን ጋር በመቀናጀት በሦሥት ዙር የመልሶ ማቋቋም ሥልጠና አግኝተው ወደ ማኅበረሰቡ መቀላቀላቸውን አንስተዋል።

አሁን ላይም በማኑፋክቸሪንግ፣ በኢንዱስትሪ እና በግብርናው ዘርፍ የሥራ ዕድል እንደተፈጠረላቸው የዘገበው አሚኮ ነው።