Search

ተመራጩ የፖለቲካ ፓርቲ የተጀመሩ ልማቶችን ማስቀጠል ይጠበቅበታል፦ የታርጫ ከተማ ነዋሪዎች

ሰኞ ሰኔ 15, 2018 57

በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አብላጫ ድምፅ አግኝቶ ያሸነፈው የፖለቲካ ፓርቲ ሀገርን እና ሕዝብን የሚጠቅሙ አጀንዳዎችን ለይቶ መሥራት እንደሚጠበቅበት የታርጫ ከተማ ነዋሪዎች ገልፀዋል።

May be an image of newsroom

 

May be an image of one or more people, tree and text

 

No photo description available.

May be an image of road, tree and newsroom

ኢቢሲ ያነጋገራቸው የከተማዋ ነዋሪዎች በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሂደት ላይ የነቃ እና ነፃ ተሳትፎ ማድረግ መቻላቸው የተሻለች ኢትዮጵያን ለመገንባት የተጣለ ጠንካራ መሠረት መሆኑን ገልጸዋል።

በምርጫው አብላጫ ድምፅ አግኝቶ ያሸነፈው የፖለቲካ ፓርቲ ሀገርንና ሕዝብን የሚጠቅሙ አጀንዳዎችን ለይቶ ከመሥራት ባለፈ፤ በየአካባቢው የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን ወደ ውጤት የመቀየር፣ ሀገራዊ ሰላም እና አንድነትን የማጎልበት ተግባር ላይ በትኩረት ሊሠራ እንደሚገባ አመላክተዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ለወጣቶች የሥራ ዕድልን የማመቻቸት፣ የኑሮ ውድነትን የማረጋጋት እና የሕግ የበላይነትን ይበልጥ የማጠናከር ሥራዎች ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ የገለጹት የታርጫ ከተማ ነዋሪዎች፤ በቀጣይ ከሚመሠረተው መንግሥት ጋር በጋራ ለመሥራት ሙሉ ዝግጁ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

በሰለሞን ባረና