በቴክኖሎጂው መስክ በየዕለቱ አዳዲስና አስገራሚ ውጤቶች እየታዩ ነው።
ትናንት በምናብ ብቻ ይታሰቡ የነበሩ ፈጠራዎች ዛሬ ወደ ተግባር ተቀይረው የሰውን ልጅ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ እያቀለሉት ይገኛሉ።
በቴክኖሎጂ እድገቷ በከፍተኛ ፍጥነት እየተራመደች በምትገኘው ቻይና በዓለም የመጀመሪያው የሆነው ‘ሃይብሪድ’ የካርጎ ድሮን የተሳካ የሙከራ በረራውን አድርጓል።

"Caihong-YH1000S” የሚል መጠሪያ የተሰጠው ይህ ዘመናዊ የካርጎ ድሮን 1.2 ሜትሪክ ቶን የመጫን አቅም አለው።
ድሮኑ ሁለት ሞተሮች የተገጠሙለት መሆኑ ለረጅም ርቀት የካርጎ በረራ ተመራጭ ያደርገዋል።
ይህ የቻይናውያን የፈጠራ ውጤት በዋናነት ለሎጀስቲክስ አገልግሎት፣ በአደጋ ጊዜ ለፈጣን ምላሽ ሰጪነት እና ለተለያዩ ተልዕኮዎች ዝግጁ ሆኖ መሠራቱን ሞደርን ቻይና ዘግቧል።
በሀብተሚካኤል ክፍሉ