Search

መላው የአፍሪካ ወንድም እህቶቻችን እንኳን ለአፍሪካ ቀን አደረሳችሁ፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ሰኞ ግንቦት 17, 2018 48

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ የሚከበረውን የአፍሪካ ቀንን ምክንያት በማድረግ፣ "ለመላው አፍሪካውያን ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን፣ እንኳን ለአፍሪካ ቀን በሰላም አደረሳችሁ" ሲሉ የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላልፈዋል።
ከ63 ዓመታት በፊት፣ አባቶቻችን እዚህ በአዲስ አበባ ተሰባስበው ነፃ እና የተባበረች አፍሪካን ለመፍጠር ደፍረው አልመው ነበር ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ያ ሕልም ዛሬም እንደ ደመቀ መሆኑን ገልጸዋል።
ዛሬ፣ እንደ ኩሩ የአፍሪካ ኅብረት መገኛ፣ ኢትዮጵያ በዚሁ የአንድነት መንፈስ ከእያንዳንዱ የአፍሪካ ሀገር ጋር በአብሮነት መቆሟንም አረጋግጠዋል።
ይሁን እንጂ ሥራዎቻችን ገና አልተጠናቀቁም። አሁን ከመፈክር ወደ ተግባር፣ ከቃል ኪዳን ወደ ዕድገት እና ብልጽግና የምንሸጋገርበት ጊዜ ነው ሲሉም አስገንዝበዋል።
“የአፍሪካ ትልቁ ሀብት ምንጊዜም ቢሆን ሕዝቦቿ ናቸው፤ አንድ ላይ ሆነን፣ ወደ ላቀ ከፍታ እንወጣለን” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ።