Search

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በቀጣይ ስምንት ወራት የሚያከናውናቸውን ዐበይት ተግባራት ይፋ አደረገ

ሰኞ የካቲት 16, 2018 81

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የተሰጠውን ተጨማሪ ስምንት ወራት የሥራ ዘመን ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችሉትን ስልታዊ የትኩረት ነጥቦች ይፋ አደረገ።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የካቲት 11 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ፣ ኮሚሽኑ ያልተከናወኑ ተግባራትን እንዲያጠናቅቅ የሥራ ዘመኑን ማራዘሙ ይታወሳል።
በዚህም መሠረት ኮሚሽኑ በቀጣዮቹ ስምንት ወራት ውስጥ የሚከተሉትን ስድስት ዋና ዋና ግቦች ለማሳካት ማቀዱን አስታውቋል፦
👉በትግራይ ክልል የምክክር ሂደት፦ በክልሉ የሚጠበቀውን የምክክር ሂደት በንቃት ማከናወን፤
👉የአጀንዳዎች ዝግጅት፦ እስካሁን የተሰበሰቡ አጀንዳዎችን በየፈርጁ ለይቶ በማዘጋጀትና በመቅረጽ ለሕዝብ ይፋ ማድረግ፤
👉የአወያዮች ዝግጁነት፦ ለሀገራዊ ምክክር ጉባኤው የሚሆኑ አወያዮችን እና አመቻቾችን መለየትና አስፈላጊውን ስልጠና መስጠት፤
👉ታላቁ የምክክር ጉባኤ፦ ሁሉንም ድምጾች የሚያስተናግድ፣ አሳታፊና አካታች የሆነ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤን ማካሄድ፤
👉የምክረ-ሀሳቦች ትግበራ፦ ከምክክሩ የሚገኙ ውጤቶችን በማጠናቀር የመፍትሔ አቅጣጫዎችን ማዘጋጀትና አፈጻጸማቸውን መከታተል፤
👉ንቅናቄና ዲጂታላይዜሽን፦ ሀገር አቀፍ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን ማስፋትና የዶክመንቴሽን ሥራዎችን በዘመናዊ የዲጂታል ዘዴ ማደራጀት።
ኮሚሽኑ ባለፉት አራት ዓመታት ለተደረገለት ሁለንተናዊ ድጋፍ ምስጋናውን አቅርቦ፣ ቀጣዩ ምዕራፍ ለሀገራዊ መግባባት ወሳኝ በመሆኑ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎና ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል።