Search

ዓድዋን የሚያህል ታሪክ ይዘን መሪዎች ወደ ሀገራችን ሲመጡ የአበባ ጉንጉን የሚያስቀምጡበት ቦታ አልነበረንም - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ማክሰኞ መጋቢት 15, 2018 47

ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት ያልተገዛችና የታላቅ ድል ባለቤት ብትሆንም፣ የውጭ ሀገር መሪዎች ወደ ሀገራችን ሲመጡ በክብር የአበባ ጉንጉን የሚያስቀምጡበት በቂ ስፍራ እንዳልነበረ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) ገለጹ።  

እንደ ዓድዋ ድል መታሰቢያ እና የታደሱት ቤተ-መንግሥታት ያሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ይህንን ታሪካዊ ክፍተት በመሙላት የሀገሪቱን ገጽታ መቀየራቸውን ጠቁመዋል።

እነዚህ የልማት ሥራዎች ቱሪዝምን ከመሳብ ባለፈ፣ ትውልዱ የሀገሩን ማንነት አውቆ በኢትዮጵያዊነቱ እንዲኮራና የአርበኝነት ስሜቱ እንዲገነባ ከፍተኛ ድርሻ እንዳላቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል።

አዲስ አበባ እንደ ኒውዮርክ፣ ፓሪስ እና ሪዮ ዲጄኔሮ ከተሞች የራሷ የሆኑ ዓለም አቀፍ መለያዎች ሊኖሯት እንደሚገባ በመጥቀስ፣ በእንጦጦና በየካ አካባቢ የተሰሩ ስራዎች ከተማዋን እንደ "ሆሊውድ" ያሉ ዓለም አቀፍ የቱሪስት መስህቦች ባለቤት እንደሚያደርጓት አመልክተዋል።

ይህ ከተማን ዘመናዊ የማድረግ ሥራ የኢትዮጵያ የክብር ታሪክ ለዓለም በሚመጥን መልኩ ለማሳየት ያለመ መሆኑንም ገልፀዋል።

በሃይማኖት ከበደ

#EthiopianBroadcastingCorporation #Ethiopia #PMAbiyAhmed #AdwaMuseum #AddisAbaba