ለዘንድሮው አረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ከስምንት ቢሊዮን በላይ ችግኞች መዘጋጀታቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ ባሰፈሩት መልዕክት፣ “የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ወቅት ላይ እንገኛለን ብለዋል።
ከስምንት ቢሊዮን በላይ ችግኞች ለተከላ ዝግጁ በሆኑበት በዚህ ወቅት፣ አረንጓዴ ለሆነች ነገ፣ ሁላችንም ተስፋን እንትከል ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።