Search

የሐዋሳ ሐይቅ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት የመጀመሪያው ምዕራፍ ግንባታ ተጀመረ

ቅዳሜ ሰኔ 06, 2018 59

የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ እና የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ጥራቱ በየነ የሐዋሳ ሐይቅ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት የመጀመሪያው ምዕራፍ ግንባታ አስጀምረዋል።

የፕሮጀክቱ ግንባታ በሦስት ምዕራፍ ተከፋፍሎ የሚከናወን ሲሆን፣ የመጀመሪያውን ምዕራፍ በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ታቅዷል።

ፕሮጀክቱ አረንጓዴ ልማት፣ የእግረኛ መንገድ፣ የብስክሌት መንገድ እና የመዝናኛ ስፍራን ጨምሮ ሌሎች መሠረተ ልማቶችን አካቶ የሚከናወን ነው።

የመጀመሪያው ምዕራፍ ግንባታ ፍቅር ሐይቅ፣ ዓሣ ገበያ እና አሞራ ገደል የሚባሉ አካባቢዎችን አጠቃልሎ የሚከናወን ሲሆን፣ ግንባታው 3.2 ቢሊዮን ብር ወጪ የሚከናወን ይሆናል።

የሐይቅ ዳር ልማት ፕሮጀክቱ ከተማዋን አዲስ ገጽታ እንደሚያላብስ እና የአካባቢውን የቱሪዝም መዳረሻነት ከፍ እንደሚያደርገው ተገልጿል።

ፕሮጀክቱ በከተማዋ ያለውን የተፈጥሮ ሀብት በማልማት፣ የቱሪዝም ኢንዱስትሪው የተሻለ ኢኮኖሚ እንዲያመነጭ የሚያስችል እንደሚሆን ተጠቁሟል።

የሐይቅ ዳር ልማት ፕሮጀክቱ 12 . የሚሸፍን እና አጠቃላይ ሥራው በማኅበረሰብ እና በመንግሥት ተሳትፎ የሚከናወን ይሆናል።

በሚካኤል ገዙ