ኢትዮጵያ በታሪኳ በርካታ ሰው ሰራሽና ተፈጥሮአዊ ፈተናዎችን ብታልፍም፣ ችግሮችን ወደ ዕድል የመቀየር ጥበቧን በተግባር እያስመሰከረች ትገኛለች። በተለይም ባለፉት ጥቂት ዓመታት ዓለም በወረርሽኝና በጂኦ-ፖለቲካዊ ውጥረቶች በታወከችበት ወቅት፣ ሀገራችን የጀመረቻቸው ስትራቴጂካዊ ስራዎች የተስፋችን ምንጭ ሆነዋል።
በመሆኑም የዛሬው የኢቢሲ ዶትስትሪም አበይት መልዕክቶች፡-
1. የምግብ ዋስትናና የስንዴ ልማት ድል
ከእርዳታ ጠባቂነት ወደ ላኪነት! በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተመዘገበው ስኬት የኢኮኖሚ ጥገኝነትን የቀነሰ ታላቅ ድል ነው። "በገዛ እጃችን መመገብ አለብን" የሚለው ጽኑ አቋም ዛሬ ፍሬ አፍርቶ ለውጭ ገበያ የሚተርፍ ምርት እንድናመርት አስችሎናል።
2. አረንጓዴ አሻራና የከተማ ውበት
ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል የአየር ንብረት ለውጥን እየተጋፈጥን ነው። ከዚህ ጎን ለጎን የሚሰሩ የኮሪደር ልማት ስራዎች ከተሞቻችንን ለነዋሪዎች ምቹ፣ ለኢኮኖሚው ደግሞ አዲስ ጉልበት እያደረጉ ይገኛሉ።
3. የተፈጥሮ ጸጋና የኢነርጂ ተስፋ
የተፈጥሮ ጋዝ ፍለጋና ልማት ስራችን የሀገሪቱን የኢኮኖሚ መዋቅር የሚቀይር ትልቅ ተስፋ ነው። ይህም ለኢንዱስትሪዎቻችን መስፋፋትና ለውጭ ምንዛሬ ግኝት መሰረት እየጣለ ነው።
4. የጽናት ተምሳሌት
በመካከለኛው ምስራቅ ያለው አለመረጋጋት በዓለም ገበያ ላይ ጫና ቢፈጥርም፣ ኢትዮጵያ የውጭ ሸቀጦችን በሀገር ውስጥ ምርት በመተካትና ብሄራዊ ጥቅሟን በማስከበር የጽናት ተምሳሌትነቷን እያስመሰከረች ነው።
በአጠቃላይ የኢትዮጵያ የብልጽግና ጉዞ በጊዜያዊ ስኬት የሚገታ አይደለም። ይህ የጽናት ጉዞ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እያንዳንዳችን በየተሰማራንበት መስክ የድርሻችንን እንወጣ!
የኢቢሲ ዶትስትሪም ኤዲቶሪያል