Search

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የግራንዴር ሴራሚክ ፋብሪካን መረቁ

ቅዳሜ ግንቦት 15, 2018 105

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) የግራንዴር ሴራሚክ ፋብሪካን መርቀው አገልግሎት አስጀምረዋል።

ይህ ግዙፍ ማምረቻ ተቋም የሀገራችንን የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ጉዞ ወደ አዲስ ምዕራፍ የሚያሸጋግር እንደሆነም ጠቅሰዋል።

ፋብሪካው ዓለም አቀፍ የጥራት እና የተወዳዳሪነት መስፈርቶችን የሚያሟሉ የሴራሚክ ምርቶችን የሚያቀርብ ነው።

ይህን ፋብሪካ ልዩ የሚያደርገው ደግሞ ለምርቶቹ ከሚያስፈልጉት ጥሬ ዕቃዎች ውስጥ 80 በመቶ በላይ የሚሆነውን ከሀገር ውስጥ አቅም ማግኘቱ እንደሆነ ነው ጠቅላይ ሚኒትሩ የገለጹት።

አክለውም "ይህ ትልቅ ስኬት ኢትዮጵያ የራሷን የተፈጥሮ ሀብትና እምቅ ጸጋ የመጠቀም ብቃቷን ከማሳደጉም ባሻገር፣ ከውጭ ገቢ ምርቶች ላይ ያለንን ጥገኝነት በከፍተኛ ደረጃ የሚቀንስ ቁልፍ እርምጃ ነው" ብለዋል።

መንግሥት ዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንቶችን በመሳብ መሰል ከፍተኛ ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸውን የፋብሪካ ግንባታዎች በመላ ሀገራችን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል።