የቻይናው ብሔራዊ አየር መንገድ ኤር ቻይና በቤጂንግ እና በሰሜን ኮሪያ መዲና ፒዮንግያንግ መካከል ተቋርጦ የነበረውን የቀጥታ በረራ ከዛሬ ጀምሮ በይፋ መጀመሩን አስታውቋል።
በአየር መንገዱ ድረ-ገጽ ላይ የወጣው መረጃ እንደሚያመላክተው፣ በረራ ቁጥር CA121 በቤጂንግ ሰዓት አቆጣጠር ማለዳ 2:05 ላይ ከቤጂንግ ካፒታል ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተነስቷል።
ይህ በረራ በሰሜን ኮሪያ የአካባቢ ሰዓት አቆጣጠር ረፋድ 5:00 ገደማ ፒዮንግያንግ አየር ማረፊያ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።
በሁለቱ ሀገራት መካከል የተጀመረው ይህ የቀጥታ በረራ በቤጂንግ እና በፒዮንግያንግ መካከል ያለውን የጉዞና የትራንስፖርት ትስስር ዳግም የሚያጠናክር መሆኑ ተመላክቷል።