Search

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአምባሳደር ቆንጂት ሥነ-ጊዮርጊስ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለፁ

ማክሰኞ መጋቢት 29, 2018 181

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ  (ዶ/ር) በአምባሳደር ቆንጂት ሥነ-ጊዮርጊስ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት የሀዘን መግለጫ መልእክት፤ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ ኢትዮጵያን በዲፕሎማሲው መስክ ያገለገሉት አምባሳደር ቆንጂት ሥነ-ጊዮርጊስ በማረፋቸው የተሰማኝን ኀዘን ለመግለጽ እወዳለሁ ብለዋል።

አምባሳደር ቆንጂት ከልጅነት እስከ ዕውቀት ኢትዮጵያን በዲፕሎማትነት በማገልገል፣ ከአምባሳደር ዮዲት እምሩ ቀጥለው ሁለተኛዋ ሴት የኢትዮጵያ አምባሳደር ናቸው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ለሕግ፣ ለአሠራር፣ ለፕሮቶኮል እና ለኢትዮጵያ ጥቅሞች በነበራቸው የጸና አቋም እናስታውሳቸዋለን ሲሉ ገልጸዋል።

አምባሳደሯ ከእርሳቸው በኋላ አያሌ ሴት ዲፕሎማቶች በመስኩ እንዲሠማሩ መንገዱን አስፍተዋል ሲሉም አመልክተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአምባሳደር ቆንጂት ሥነ-ጊዮርጊስ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀው፤ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለሥራ ባልደረቦቻቸው እና ለመላ ኢትዮጵያውያን መጽናናት ተመኝተዋል።