Search

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ፕሬዝዳንት ቄስ ደረጀ ጀምበሩ በዓለ ትንሣኤን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ አባታዊ መልዕክት አስተላለፉ

ቅዳሜ ሚያዝያ 03, 2018 80

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ፕሬዝዳንት ቄስ ደረጀ  ጀምበሩ በዓለ ትንሣኤን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ አባታዊ መልዕክት አስተላለፉ

ከኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል የተላለፈ 2018 . የትንሣኤ በዓል መልክት

በስመ አብ፤ በስመ ወልድ፤ በስመ መንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ አሜን!

በጌታ የተወደዳችሁ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር የምትኖሩ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ምዕመናን፤ የክርስትና እምነት ተከታዮች እና ኢትዮጵያውያን ወገኖች በሙሉ፤

ከምህረቱና ከቸርነቱ የተነሳ ሁላችሁንም በሰላምና በጤና ጠብቆ እንኳን 2018 .. የትንሣኤ መታሰቢያ በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን በማለት በራሴና በኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ስም መልካም ምኞቴን ስገልጽ በደስታ ነው፡፡

የትንሣኤን መታሰቢያ በዓል ስናከብር፤ በክርስቶስ ኢየሱስ መከራና ስቃይ፣ ሞትና ትንሣኤ ያገኘነውን የዘላለም ሕይወት እንዲሁም፤ እግዚአብሔርበአንድያ ልጁ በኩል የገለጸውን ወደር የሌለውን ፍቅሩን እያሰብን፤ ዕለቱን እግዚአብሔርን በተሰበረ ልብ በማምለክና በማመስግን ማሳለፍ ይገባናል፡፡ አሁንም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስፋሲካችን" ሆኖ፤ በመስቀል ላያ ባፈሰሰው ደሙ ከኃጢያትና ከዘላለም ሞት በመዋጀት፤ ልጆቹ ስላደረገን፤ በጽኑ ተስፋው ተደላድለን ቆመናልና ክብርና ምስጋናን ለእርሱ ይሁን፡፡

ሐዋሪያው ዮሐንስ በመልእክቱ፤ ‹‹ወዳጆች ሆይ፤ ፍቅር ከእግዚአብሔርስለሆነ፤ የሚወደውም ሁሉ ከእግዚአብሔር ስለተወለደ፤ እግዚአብሔርንም ስለሚያውቅ፣ እርስ በርሳችን እንዋደድ›› (1ዮሐንስ 4:7-11) በማለት እንዳስተማረው፣ ትንሳኤ፣ ጥላቻ በፍቅር፤ መለያየት በአንድነት፤ ሐዘን በደስታ፤ እንዲሁም ሽንፈት በድል የተደመደመበት ስለሆነ በእኛም መካከል ጎልቶ መታየት ያለበት ፍቅር፣ ሰላምና ይቅርባይነት ነው፡፡ ይህም በፍጹም ቅንነት፤ መከባበርና መደማመጥ፤ በእርቅ የሀገራችንን ሰላም በአስተማማኝ ሁኔታ ለማረጋገጥና የሕዝባችንንም አንድነት በጽኑ ዓለት ላይ ለማቆም ያስችለናል፡፡

በመካከላችን አሉ የሚበሉ ልዩነቶችን፤ በማስተዋልና በጥበብ ለመፍታት፤ ብሎም የበደልናቸውን ብቻ ሳይሆን የበደሉንንም በይቅርታ ለመቀበልና እውነተኛ ሰላም ለማስፈን ብንሠራ፣ ጥላቻ እየደበዘዘ ፍቅር ግን እየጎለበተ ይሄዳል፡፡ ሀገራችንም ከዕድገት ወደ ዕድገት ትሸጋገራለች፡፡ ያን ጊዜ ወጣት ልጆቻችን የሚሰደዱባት ሳይሆን ሠርተው የሚበለጽጉባት፤ እናት ልጆቹዋን ይዛ ለልመና መንገድ ላይ የማትወጣባት፤ ይልቁንም ሕዝቦቹዋ የሚኮሩባት ከድህነት የተላቀቀች ሀገር ትሆናለች፡፡

ስለዚህ በዕለት ተዕለት ተግባራችን ለእርስ በርሳችንና ለሕዝባችን ያለንን እውነተኛ ፍቅር በይቅርታና በመቀባበል መግለጥ ይኖርብናል፡፡ በመሆኑም በወንድማማች ፍቅር፤ ልብ ለልብ ተሳስረን፤ ለጋራ ጥቅምና ዕድገት፤ አስተማማኝ ሰላምን ለማስፈን በጽናት እንቆም ዘንድ ጥሪያችንን በትህትና እናስተላልፋለን፡፡

በተለይም በዚህ ዓመት በሚካሄደው ሀገራዊ ምርጫ፣ የዜግነት መብታችን እንደመሆኑ፣ በንቃት መሳተፍና ምርጫው በሰላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ሁሉ ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡ ከዚህ በፊት እንዳደረግነው ሁሉ አሁንም ምርጫው በሰላም ተጀምሮ በሰላም እስከሚጠናቀቅ ድረስ፤ ሁሉም አብያተ ክርስቲያናት፤ በእግዚአብሔር ፊት በጸሎት እንዲቆዩ አደራ ለማለት እንወዳለን፡፡እግዚአብሔር በቃሉ ‹‹ለድሃ፣ ቸርነትን የሚያደርግ፤ ለእግዚአብሔርያበድራል፤ በጎነቱንም መልሶ ይከፍለዋል›› (መጽሐፈ ምሳሌ 229) ስለሚል፤ የክርስቶስ ኢየሱስን ትንሳኤ ስናከብር፤ በመካከላችን በልዩ ልዩ ችግር ውስጥ ያሉትን ወገኖች በማሰብ፣ እነርሱም ከእኛ ጋር የደስታችን ተካፋዮች ይሆኑ 113.8 ከፍቅር የመነጨ ልግስና እንድናደርግላቸው በጌታ ፍቅርእናሳስባለን፡፡

በተለይም በደቡብ ኢትዮጵያ፤ በጋሞ ዞን፣ አንዳንድ ደጋማ ሥፍራዎች በተከሰተው ከፍተኛ ዝናብ እንዲሁም የመሬት መንሸራተት 125 ወገኖቻችንን በሞት ያጣንና በብዙዎችም ላይ የአካል ጉዳትና የንብረት ውድመት የደረሰ ሲሆን ከፍታኛ ቁጥር ያለው ህዝብ ተፈናቅሎ በመጠለያ ውስጥ ይገኛል፡፡

በመሆኑም ሕዝባችን በታላቅ ሐዘን ውስጥ ስለሚገኝ፤ በዚህ ወሳኝ ወቅት ስጦታችንን በተደራጀ ሁኔታ በማሰባሰብ፤ የሐዘናቸው ተካፋዮች መሆናችንን በተግባር እንድንገልጽ በራሴና በኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ስም አደራ እያልኩ፤ የደስታና የሰላም በዓል ይሆንላችሁ ዘንድ ጸሎቴም ምኞቴም ነው፡:

እግዚአብሔር ሕዝባችንና ሀገራችንን ይባርክ!

ሰላሙንም ያብዛልን፡፡ አሜን!

ቄስ ደረጀ ጀምበሩ

የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ፕሬዚዳንት