Search

“ይበጀኛል የምለውን ለመምረጥ ጓጉቻለሁ”፦ የ18 ዓመቷ ሰላም ደመቀ

ሓሙስ ሚያዝያ 08, 2018 98

የባህር ዳር ከተማ የ7ኛው አጠቃላይ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ እየተከናወነ ሲሆን ነዋሪዎች ወደ ምርጫ ጣቢያዎች በመሄድ በመመዝገብ ላይ ናቸው።
ከእነዚህ መራጮች መካከል አንዷ የሆነችው እድሜዋ 18 የሞላት ሰላም ደመቀ ለመጀመሪያ ጊዜ በጠቅላላ ምርጫው ድምፅ ለመስጠት የምርጫ ካርድ ወስዳለች፡፡
ለሰላም ደመቀ ይህ ምርጫ ለመጀመሪያ ጊዜ በሀገር ጉዳይ ላይ ድምፅ የምትሰጥበት የታሪኳ ምዕራፍ በመሆኑ ልዩ ትርጉም የሰጠችው ነው።
ዕድሜዋ ለመራጭነት በመድረሱና ለመጀመሪያ ጊዜ የመምረጥ መብቷን የሚያረጋግጥላትን ካርድ በመያዟ ያላትን ደስታ ለኢቲቪ ገልጻለች።
ሰላም የያዘችው የምርጫ ካርድ ለእሷ የመምረጥ መብት ብቻ ሳይሆን፣ የነገዋን ኢትዮጵያ በመቅረፅ ሂደት ውስጥ ተሳታፊ የሆነችበት የሉዓላዊነት ጉዞ መጀመሪያ ነው።
ዕድሜያቸው ለመምረጥ የደረሱ ዜጎች ሁሉ ካርዳቸውን በወቅቱ በማውጣት ለሀገራቸው የዴሞክራሲ ልምምድ የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪዋን አስተላልፋለች።
በሳሙኤል ወርቅአየሁ