Search

ለኢትዮጵያ ክብር በጽናት የቆመ!

ዓርብ ሰኔ 05, 2018 60

 

የኢትዮጵያ ስም በዓለም አደባባይ በክብር ሲነሳ፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ስምም ምንጊዜም ከፊት ይመጣል። ይህ የጀግኖች ስብስብ መደበኛ ወታደራዊ ግዳጅን ብቻ የሚወጣ ሀይል ሳይሆን፣ የኢትዮጵያ ህልውና ጠበቃ፣ የትውልድ አደራ ተረካቢ፣ የኢትዮጵያ ክብር ዘብና  ፅኑ ምሰሶ ነው። ከትላንት እስከ ዛሬ፣ በዘመናት መሃከል አደራውን ሳይተው ለእናት ሃገሩ  በፈተና፣ በአውሎ ንፋስና በማዕበል ውስጥ እያለፈ፣ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ከፍ አድርጎ ያውለበለበ፣ በህይወቱ ኢትዮጵያን የሚያፀና ታማኝ የቁርጥ ቀን ልጆች ስብስብ ነው።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከዘመናት በፊት ጀምሮ የአባቶቹን አኩሪ የጀግንነት እና የአርበኝነት ወኔ በመውረስ፣ በየዘመናቱ የተቃጡባትን የውጭ ወረራዎች እና የውስጥ የባንዳ ሴራዎችን በማክሸፍ የሀገርን ክብር ያስጠበቀ ህያው ጋሻ ነው። የዓድዋን የድል መንፈስ፣ ወርሶ የዘመናችንን የህልውና ዘመቻዎች በድል አጠናቆ ያሳየው ይህ ሰራዊት፣ ኢትዮጵያ እንዳትፈርስ የከፈለው ዋጋ በቃላት የሚገለፅ አይደለም። በረሀውን አቋርጦ፣ ቆላውን ተራምዶና ደጋውን ወጥቶ፣ ለራሱ ህይወት ሳይሳሳ ለሀገሩና ለህዝቡ ሲል በደሙ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት አትሞ ያቆየ የክብር ዘብ ነው።

በዘመናት ጉዞው ሁሉ በርካታ ፈተናዎች ቢገጥሙትም፣ የዛሬው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከወትሮው በተለየ የላቀ የለውጥ (ሪፎርም) እና የዘመናዊነት ምዕራፍ ውስጥ ይገኛል። ትላንት በአካላዊ ጥንካሬ፣ በሞራል እና በሀገር ፍቅር ስሜት ብቻ ሲዋጋ የነበረው ሰራዊት፣ ዛሬ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ፣ በሳይበር ደህንነት አቅም፣ በእውቀትና በላቀ የጦር ስልት የተደራጀ ሆኗል። ይህ አቅሙ ደግሞ የውጭ ታሪካዊ ጠላቶችም ሆኑ የውስጥ የፖለቲካ ቁማርተኞች ሀገርን ለማፍረስ የሸረቡትን ማንኛውንም የጥፋት ሴራ በእንጭጩ እንዲያመክን አድርጎታል።

ሰራዊቱ የሀገራችንን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ በሚያደርገው ተጋድሎ፣ የማስቀረትና የመከላከል (Deterrence) አቅሙን በማሳደግ፣ ጠላት ኢትዮጵያን ለመድፈር ሲያስብ የሚከፍለውን ዋጋ ተረድቶ እንዲሸሽ የሚያደርግ ባለግርማ ሞገስ አቅም ገንብቷል።

የዚህ ሰራዊት ሌላው እጅግ አስደናቂ ገፅታ ውብ ህብረብሔራዊነቱ ነው። ከሁሉም የኢትዮጵያ ማዕዘናት የተውጣጡ፣ የቋንቋ፣ የባህል እና የሀይማኖት ሕብር ተላብሶ "ኢትዮጵያዊነት" በሚለው ትልቅ ማዕቀፍ ውስጥ የተሳሰሩ ጀግኖች ናቸው።

እነሱ በግንባር ደማቸውን ሲያፈሱና አጥንታቸውን ሲከሰክሱ፣ ኢትዮጵያውያን በሰላም ወጥተው ይገባሉ፤ ሀገራችንም የጀመረችውን የማክሮ ኢኮኖሚ፣ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ልማት ጉዞ ያለ ስጋት በፅናት ታስቀጥላለች። 

በአጠቃላይ፣ "ለኢትዮጵያ ክብር የቆመ!" ስንል፣ የትላንቱን ታሪክ ጠብቆ፣ የዛሬውን አውዳሚ ፈተና ተሻግሮ፣ የነገዋን ብሩህና የበለፀገች ኢትዮጵያ በፅኑ መሰረት ላይ ለማቆም ሌት ተቀን የሚተጋውን ጀግና ሀይል ማለታችን ነው። ይህን የክብር ዘብ፣ የልማት አጋዥ እና የሰላም አለኝታ የሆነ ሰራዊት ማክበር፣ መደገፍ እና ከጎኑ መቆም የሁሉም ኢትዮጵያዊ ታሪካዊ እና ሀገራዊ ግዴታ ነው። የማይበገረው የኢትዮጵያ ክንድ ለዘላለም የሀገራችንም የጀመረችውን የማክሮ ኢኮኖሚ፣ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ልማት ጉዞ ያለ ስጋት በፅናት ታስቀጥላለች።ርን ክብር እንደጠበቀ፣ የኢትዮጵያን ከፍታ እንዳረጋገጠ ይኖራል!