Search

በስሉጥ ከተማ፤ ስሉጥ አገልግሎት - አዲስ መሶብ!

ዓርብ ሰኔ 05, 2018 46

ከቅርብ  ዓመታት ወዲህ፣ በከተማችን ከታየው አስደማሚ የከተሜነት ትራንስፎርሜሽን ጎን ለጎን የህበረተሰብ ተጠቃሚነትን ማዕከል ያደረጉ ዘመን ተሸጋሪ ሰው ተኮር ስራዎች ተሰርቷል፤ እየተሰሩም ይገኛሉ፡፡ ከነዚህ ውስጥ የህዝባችን የዘመናት ጥያቄ የነበረውን የአገልግሎት አሰጣጥ ጉድለት ስር-ነቀል የሆነ ለውጥ ለማምጣትም መጠነ ሰፊ የሆነ የመሰረተ-ልማት እና የሰው ሃይል ልማት እየተሰራ ይግኛል፡፡

ዕድገቷን እና ስሉጥ ከተማነቷን (Smart-city) የሚመጥን አገልግሎት ለማቅረብ ቴክኖሎጂን ግብር ላይ የማዋል ሂደት አጠናክራ ይዛለች፡፡ ይኸውም የመሶብ አንድ ማዕከል ዲጂታል አገልግሎት ቀዳሚው ተጠቃሽ ነው፡፡

አዲስ መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት፣ በከተማችን ሁሉም ክፍለከተሞ ተደራሽ በማድረግ የህብረተሰቡን የአገልግሎት አሰጣጥ ለማዘመን ቀን ከሌሊት እየተሰራ ይገኛል፤ የላቀ ውጤትም ተመዝግቦበታል፡፡

እስከአሁን በማዕከል እና በዘጠኝ ክፍለ-ከተሞች እንዲሁም፣ በተንቀሳቃሽ አውቶብስ የተደራጀ፣ ጥብቅ ክትትልና ድጋፍ የሚደረግባቸው፣ የበቁ የሰው ሃይል የተማላላቸው ማዕከሎች አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡

በቴክኖሎጂ በታገዘ በተደረገ ዳሰሳ እንደሚያሳየው ተገልጋዩ ከ99 በመቶ በላይ እርካታ ያመላክታል፡፡ ቀሪ ሁለት ክፍለ-ከተሞችም ግንባታቸው ተጠናቆ በጥቂት ቀናት አገልግሎት ይጀምራሉ፡፡

የአገልግሎት አሰጣጥ ጉድለትን ታሪክ ለማድረግ በቁርጠኝነት ተግብረን፣ የህብተሰባችንን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማላቅ አበክረን እንሰራለን!