Search

ገዳ ሜልባ ለአዲሱ ገዳ ሙደና ስልጣን አስረከበ

እሑድ ሰኔ 07, 2018 56

በታሪካዊውና ጥንታዊው የገዳ ሥርዓት እሴት መሠረት፣ የቱለማ ገዳ የስልጣን ሽግግር ሥነ-ሥርዓቱን በዛሬው ዕለት አከናውኗል።

 በዚህም መሠረት ላለፉት ስምንት ዓመታት በሜልባ ገዳ ዘመን (በአባ ገዳ ጎበና ሆላ) ሲመራ የነበረው የቱለማ ገዳ፣ ስልጣኑን ለአዲሱ ገዳ አስረክቧል።

የዘመነ ሜልባን ማጠናቀቅ ተከትሎ፣ የገዳ ሥርዓቱን የሉዓላዊነትና የሥልጣን ምልክት የሆነውን "አለንጋ" በመረከብ የቱለማ አባ ገዳ ሆነው የተሰየሙት የሙደናው አባ ገዳ ጌቱ ተሊላ ናቸው። 

ሥልጣናቸውን በስኬት ያጠናቀቁት የቀድሞው አባ ገዳ ጎበና ሆላ ደግሞ፣ በሥርዓቱ ደንብ መሠረት ወደ "ዩባ" (አማካሪነት) ደረጃ በመሸጋገር አዲሱን አመራር በምክርና በዕውቀታቸው ማገልገላቸውን ይቀጥላሉ።