Search

ለኪነ-ጥበብ ልዩ ትኩረት የሰጠችው መዲናችን

እሑድ ሰኔ 07, 2018 45

አዲስ አበባ የበርካታ ከያኒያን መፍለቂያ ከተማ ብትሆንም ሙያተኞችን እና ታዳሚውን የሚመጥን የጥበብ መመልካቻና መታደሚያ ስፍራ እብዛም አልነበራትም ከለውጡ በፊት የነበሩ ቲያአትር እና ሲኒማ ቤቶች እርጅና የተጫናቸው ከመሆናቸው በተጨማሪ የጥበብ ቤተሰቦችን የማይመጥኑ ነበሩ። ከለውጡ በኃላ በተከናወነው ዘርፈ ብዙ የልማት ስራ በተለይም በከተማዋ በሚከናወኑ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ለዘርፉ ልዩ ትኩረት በመስጠት በርካታ አምፊ ቲያአትር ቤቶችና ሲኒማ ቤቶች መገንባት ተችሏል።

ለአብነትም በቅርቡ ግንባታቸው ተጠናቆ ለህዝብ ክፍት የተደረጉ የህፃናት እና ወጣቶች ቲያአትር ቤት እንዲሁም የአዲስ ሲኒማ ኮንፕሌክስ እና በአደዋ ሙዚየም ውስጥ የሚገኘው ስማርት ሲኒማ ቤት ጨምሮ በተለያዩ የከተማ አካባቢዎች የተገነቡ ታላላቅ ሁነቶቸን ማስተናገድ የሚችሉ ግዙፍ ስፍራዎች ለዚህ አይነተኛ ማሳያ ናቸው፡፡

የነዚህ አንፊ ቲያአትር ቤቶቸ እና ሲኒማ ቤቶች ግንባታ ለጥበበኞች የፈጠራ መፍለቂያ ከመሆን ባለፈ በኢትዮጵያ የኪነጥበብ ኢንዱስትሪ አዲስ ታሪክ መፃፍ የቻሉ እንዲሁም ከያኒያን ስራዎቻቸውን በዓለም አቀፍ ጥራት ለተመልካች ማቅረብ እንዲችሉ ዕድል የከፈቱ ናቸው፡፡

በተጨማሪም ለከተማዋ ነዋሪዎችና ጎብኚዎች ጥበብን በከፍተኛ ጥራትና በምቾት የሚታደሙበት ልዩ መዳረሻ መሆን ችለዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ልማት ሁለንተናዊ መሆኑን በመገንዘብ አሁንም በሚሰራቸው የልማት ስራዎች ሁሉን አካታችነት ላይ ቅድሚያ ሰጥቶ በትኩረት መስራቱን ይቀጥላል።