Search

ኢቢሲ ከቲቪ ብሪክስ ጋር የትብብር ስምምነት ተፈራረመ

ረቡዕ ሰኔ 10, 2018 117

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) በዓለም አቀፉ የብሪክስ የመረጃ መረብ ውስጥ ያለውን ተሳትፎ ለማጠናከር ከቲቪ ብሪክስ (TV BRICS) ጋር የትብብር ስምምነት ተፈራርሟል።

ስምምነቱን የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ቢኒያም ኤሮ እና የቲቪ ብሪክስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጃና ቶልስቲኮቫ ተፈራርመውታል።

በስምምነቱ መሠረት ሁለቱ ተቋማት የመረጃ፣ የልምድ እና የባለሙያ ልውውጥ የሚያደርጉ ሲሆን፣ የብሪክስ አባል ሀገራትን ትብብር ይበልጥ የሚያጠናክሩ የሚዲያ ይዘቶችን በጋራ ያመርታሉ።

በምክትል ሥራ አስፈጻሚ ማዕረግ የዋና ሥራ አስፈጻሚ /ቤት ኃላፊ አቶ ሞላልኝ መለሰ ስምምነቱ የኮርፖሬሽኑን ጋዜጠኞች የሙያ አቅም ለማሳደግ ጉልህ ድርሻ እንዳለው ገልጸዋል።

የቲቪ ብሪክስ የአፍሪካ ቀጣና ኃላፊ ዩሊያ ናዛርኪና በበኩላቸው የኢቢሲ ባለሙያዎች ልምድ የብሪክስን የመረጃ አጀንዳ ይበልጥ እንደሚያበለጽገው አረጋግጠዋል።

ይህ የትብብር ማዕቀፍ ኢትዮጵያ ወቅታዊ እና ትክክለኛ መረጃዎችን ከብሪክስ ሀገራት በቀጥታ እንድታገኝ፣ እንዲሁም ሀገራዊ አጀንዳዋን፣ የአፍሪካን ብዝኃ ባህል እና የኢንቨስትመንት አማራጮችን በዓለም አቀፍ የሚዲያ መድረኮች በስፋት እንድታስተዋውቅ ሰፊ ዕድል ይፈጥርላታል።

በለሚ ታደሰ