Search

በትንሹ ጥረት ወደ ታላቅ ሀገራዊ ለውጥ፤ ለትውልድ የሚሻገር አረንጓዴ ዐሻራ

ቅዳሜ ሰኔ 13, 2018 42

ዛሬ የምንተክላት እያንዳንዷ ችግኝ ነገ የምናያትን ለምለምና ውብ ኢትዮጵያን ለመገንባት የምንጥለው ጠንካራ የመሠረት ድንጋይ ናት።
የአየር ንብረት መዛባትን መቋቋም፣ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ እና የተፈጥሮ ሚዛንን መጠበቅ በአንድ ቀን የሚሳኩ ባይሆኑም የእያንዳንዳችን ትንሽ ጥረት ተደምሮ በጊዜ ሂደት ትልቅ ሀገራዊ ለውጥ ያመጣል።
የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ተራ የዛፍ ተከላ ብቻ ሳይሆን ለተፈጥሮ የምንሰጠው ታላቅ ቃልና ለመጪው ትውልድ የምናስቀምጠው ሕያው ቅርስ ነው።
May be an image of railroad
ዛሬ ጉድጓድ ቆፍረን የምንተክላት ችግኝ ነገ አድጋ የአፈር መሸርሸርን በመከላከል እና የከርሰ-ምድር ውኃ እንዲጎለብት በማድረግ የተፈጥሮ ሀብትን ትጠብቃለች።
የፍራፍሬና ዘላቂ ጠቀሜታ ያላቸው ዛፎች ደግሞ ለወደፊት የምግብ ዋስትና እና ለኢኮኖሚ አቅም መሠረት ይሆናሉ።
ይሁን እንጂ የዚህ ታላቅ ሥራ ትክክለኛው ውጤት የሚመጣው ችግኝ በመትከል ብቻ ሳይሆን እንዲጸድቁና እንዲያድጉ በኃላፊነት ስሜት በመንከባከብ ጭምር ነው።
ይህም ችግኞችን በአመቺ ቦታዎች መትከልን፣ ውኃ መስጠትን እና ከአደጋ መጠበቅን ያካትታል።
ዛሬ የምናደርገው የጥቂት ደቂቃዎች ጥረት ነገ በሀገር ላይ የሚታይ ታላቅ ለውጥ ስለሚያመጣ፣ አረንጓዴ ዐሻራችንን ዛሬውኑ በማሳረፍ የነገዋን ለምለም ኢትዮጵያ በጋራ እንገንባ።