Search

የመደመር አንቀጽ

ሰኞ ሰኔ 15, 2018 43

በዓለም ላይ ቀጣይ የሀገራት ሕልውና የሚመሠረተው፤ ያልታወቁና ያልተገመቱ አደጋዎችን ለመቆጣጠርና፤ በአደጋ ውስጥ አሸንፎ ለመውጣት ባላቸው ዝግጁነት ልክ ነው።

ያለንበት ዘመን ነገሮች አይገመቴ የሆኑበትና በቶሎ የሚለዋወጡበት፤ የሰው ልጆች የሚሠሯቸው ሥራዎችና ቴክኖሎጂዎች ወዴት እንደሚያመሩ በግልጽ የማይታወቅበት ነው።

አስቀድሞ ዝግጅት ማድረግና፤ ከዓለም ሁኔታ ጋር በፍጥነት እየተላመዱ መሄድ የግድ እንደሆነ መገንዘብ እንችላለን።

ስለሆነም የነገዋ ኢትዮጵያ ከአሁን በፊት የገጠሙንንም ሆነ፤ እስካሁን ያልገጠሙንን አደጋዎች አስቀድመው ለመከላከል ዝግጁ የሆኑ ልጆች ይኖሯታል።

ስለ ለገ አስቀድመው የሚተልሙና ስለዘላቂ ሕልውና መላ የሚያበጁ፤ ሙሽራው ከመምጣቱ በፊት በርበሬ አዘጋጅተው የሚጨርሱ፤ችግሮች ከመከሠታቸው በፊት እንዲከሥሙ መፍትሔ የሚያዘጋጁ፤ የፊት የፊቱን ብቻ ሳይሆን የሩቁን እያሰቡ የሚራመዱ፤ ከትናንት እና ከዛሬ የተማሩ ልጆች ይደርሱላታል።

ድርቅ በድጋሚ እንዳይጎበኘን የሚያደርጉና፤ ተፈጥሮን ለማደስ የሚረዱ ሥራዎች፤ የነገው ትውልድ ባህል ይሆናሉ።

የመደመር ትውልድ

ገጽ - 95/96