• የታሪክ ክብር መመለስ፡- ደብረ ማርቆስ ከ70 ዓመት በፊት በኢትዮጵያ ቀዳሚ ከተማ እንደነበረች ሁሉ፣ አሁንም ያንን የቀድሞ ክብሯንና የብልጽግና ተምሳሌትነቷን ልትመልስ ይገባል።
• የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት፡- ለ30 ዓመታት ተቋርጦ የነበረው የአውሮፕላን ማረፊያ አገልግሎት ዳግም መጀመሩ፣ ለንግድ፣ ለኢንቨስትመንትና ለቱሪዝም ዘርፍ ከፍተኛ ፋይዳ አለው።
• የሰላም አስፈላጊነት፡- ከተማዋ የወሎና የወለጋ ድልድይ ሆና የኖረችበትን የታሪክ ክብር ለማስቀጠል፣ ለሰላም ቅድሚያ መስጠትና በሰላማዊ መንገድ መነጋገር የሁላችንም ግዴታ ነው።
• የሽፍታ እንቅስቃሴን ማውገዝ፡- የሰዎችን በነፃነት የመንቀሳቀስና የመሥራት መብት የሚጋፉ የሽፍታ እንቅስቃሴዎች በአካባቢው ላይ የሚፈጥሩት ስጋት ተቀባይነት የለውም፤ ማኅበረሰቡ ከጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ሰላሙን መጠበቅ አለበት።
• የመከፋፈል አደገኛነት፡- በዘር፣ በጎጠኝነትና በጽንፈኝነት መከፋፈል ሀገርን ከመጉዳት ውጪ ፋይዳ የለውም፤ ቤተሰብንና የአንድ እናት ልጆችን ሳይቀር የሚነጣጥል ይህ ክፉ ልምምድ ሊቆም ይገባል።
• የልማት ቁርጠኝነት፡- ልማት ትዕግሥት፣ ጊዜና ትብብርን ይፈልጋል፤ መንግሥት የሕዝብን የልማት ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ ለመመለስ እና የጀመራቸውን ሜጋ ፕሮጀክቶች በጥራት ለማጠናቀቅ ቁርጠኛ ነው።
• የውይይት በር ክፍት ነው፡- የመንግሥት በርና ልብ ለሀገር ሰላም፣ ለልማትና ለጋራ ብልጽግና ለመወያየት ሁልጊዜም ክፍት ነው።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: