Search

ከኢራን ጋር የነበረው የተኩስ አቁም ስምምነት ቢያበቃም አሜሪካ ከኢራን ጋር ትወያያለች፦ ፕሬዝዳንት ትራምፕ

ዓርብ ሐምሌ 03, 2018 120

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ድርድሩ እንዲቀጥል ጥያቄ ማቅረቧን ገልጸው፣ አሜሪካም ይህንን ውይይት ለመቀጠል መስማማቷን አስታውቀዋል።

ይሁን እንጂ ፕሬዝዳንቱ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባወጡት መግለጫ፣ ከዚህ ቀደም የነበረው የተኩስ አቁም ስምምነት "ማብቃቱን" አውጀው፤ አሜሪካ አቋሟን ለኢራን በግልጽ ማሳወቋን ተናግረዋል።

ይህ የትራምፕ መግለጫ የተሰማው፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ለቀናት የዘለቀውን ተከታታይ የጥቃት ልውውጥ ተከትሎ ወታደራዊ ውጥረቱ እጅግ በተባባሰበት በአሁኑ ወቅት ነው።

የኢራን ባለስልጣናት ለፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተያየት እስካሁን በይፋ የሰጡት ምላሽ የለም።