ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የደብረ ማርቆስ አውሮፕላን ማረፊያን መርቀው በከፈቱበት ወቅት እንደተናገሩት አዲሱ አውሮፕላን ማረፊያ በቀን ሶስት ጊዜ በረራዎችን በማስተናገድ የአካባቢውን የትራንስፖርት ትስስር ያቀላጥፋል።
ደብረ ማርቆስ በ1951 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ከነበሩ 20 ቀዳሚ ከተሞች አንደኛ ወጥታ የነበረችና ቀደምት የቴክኖሎጂና የትምህርት መሠረተ ልማቶች የገቡባት ከተማ መሆኗን ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህ አውሮፕላን ማረፊያ መገንባቱ ከተማዋ የነበራትን የቀድሞ ዝና እና ክብር እንድታድስ ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥርላት ጠቁመዋል።
ልማት የራሱ የሆነ ጊዜ፣ ሃብትና ጥበቃ የሚሻ ሂደት መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አውሮፕላን ማረፊያው በተሳካ ሁኔታ ተጠናቅቆ ለምርቃት መብቃቱ ለምድሪቱም ለሰማይም ትልቅ ደስታ ነው ብለዋል።
በምርቃቱ ላይ የኢፌድሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰውን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: