Search

ለሰላምና ለልማት ሲባል በሰለጠነ የፖለቲካ አግባብ መነጋገር ይገባል፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

እሑድ ሐምሌ 05, 2018 33

ለዘላቂ ሰላምና ልማት ሲባል የሚያለያዩን ጥቃቅን ጉዳዮችን ወደ ጎን በመተው በሰለጠነ የፖለቲካ አግባብ መነጋገርና መወያየት እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አሳስበዋል።

መንግሥት ለሰላምና ለውይይት ያለው በር ምንጊዜም ክፍት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ  በድጋሚ አረጋግጠዋል።

ዜጎች የሚያለያዩትን ጥቃቅን ጉዳዮች በመተው የጋራ መሻት በሆኑት ሰላምና ልማት ላይ ሊተባበሩ እንደሚገባ ጠቅሰው፣ ከውይይት ውጪ ያለው አማራጭ ሀገርንና ሕዝብን ከመጉዳት ባለፈ አንዳች ጥቅም እንደማያስገኝ አስገንዝበዋል።

ሕዝቡ በተለያዩ የታሪክ አጋጣሚዎች በርካታ ትግልና ፍልሚያዎችን ማለፉንና ከእነዚህ ጦርነቶች የተገኘው ውጤት ሞትና ኪሳራ ብቻ እንደነበር በማስታወስ “አሁን ሊበቃን ይገባል፤ ያንን በጋራ መወሰን አለብን” ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ልማት ልክ እንደ እንቁላል ጫጩት የራሱ የሆነ ሙቀት፣ ጥበቃና ጊዜ የሚሻ ሂደት መሆኑን በምሳሌ ያስረዱት ጠቅላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣  ዜጎች በትዕግሥት፣ በሕዝባዊ ትብብርና በተደመረ መንፈስ ለልማት እንዲነሱ አደራ ብለዋል።

ለቀጣይ ትውልድ የተሻለች ሀገር ለማስረከብ በታሪክ ላይ ቆመን መልካም መልካሙን መውሰድና የጎደሉትን በጋራ መሙላት ይገባናልም ብለዋል።

በመሐመድ ፊጣሞ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: