Search

በ75ኛው የዓለም ቁንጅና ውድድር ኢትዮጵያን ወክላ የተሳተፈችው ሩት ይርጋለም ወደ ሀገሯ ስትመለስ አቀባበል ተደረገላት

ማክሰኞ ጳጉሜን 03, 2018 227

75ኛው የዓለም ቁንጅና ውድድር (Miss World 2026) ኢትዮጵያን ወክላ የተሳተፈችው ሩት ይርጋለም ወደ ሀገሯ የተመለሰች ሲሆን በቦሌ ዓለም አቀፍ  አውሮፕላን ማረፊያ ስትድርስ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላታል፡፡

ሩት ይርጋለም 75ኛው የዓለም ቁንጅና ውድድር (Miss World 2026) ወደ ቶፕ 40 ሳታልፍ ብትቀርም፣ 3 ሚሊዮን በላይ የህዝብ ድምፅ በማግኘት የነበራትን ትልቅ ቦታ አረጋግጣለች።

በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ስትደርስ በተደረገው የአቀባበል ስነ-ስርዓት ላይ ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የተወከሉ ከፍተኛ  የስራ ሀላፊዎች ቤተሰቦቿ እና አድናቂዎቿ ተገኝተዋል።

በስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የሩት አባ አቶ ይርጋለም ወልደሥላሴ "በአንዷ ልጄ አሰቃቂ ህልፈት እጅግ ተሰብሬ ነበር፤ ነገር ግን መላው  የኢትዮጵያውያን ለሩት ያሳዩት  ፍቅርና ድጋፍ ዳግም ቆሜ እንድሄድ ብርታት ሆኖኛል" ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ሩት በበኩሏ በዓለም አቀፍ መድረክ ሀገሯን ወክላ መቆሟ በራሱ ትልቅ ድል መሆኑን በመግለጽ፣ የእህቷን ህልፈት ወደ ጥንካሬ በመቀየር በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ለመታገል የጀመረችውን ንቅናቄ አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጣለች።

በዳዊት ጣሰው

 

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: