Search

"የመተሳሰብ እና የመረዳዳት ባህላችን ከበዓላት ውጪም በዘላቂነት ሊቀጥል ይገባል" - አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር

ረቡዕ ጳጉሜን 04, 2018 28

የኢትዮጵያውያንን የመረዳዳት እና የመተሳሰብ ባህል ከበዓላት ወቅት አሻግሮ፣ በዕለት ተዕለት ሕይወትም በተጠናከረ መልኩ መቀጠል እንደሚገባው የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር አሳሰቡ።

አፈ ጉባኤው ይህንን ያሉት፣ 2019 . አዲስ ዓመትን አስመልክቶ በምክር ቤቱ ጽሕፈት ቤት ለሚሠሩ ዝቅተኛ የወር ገቢ ላላቸው ሠራተኞች የበዓል መዋያ ድጋፍ ባደረጉበት ወቅት ነው።

ድጋፍ ማድረግ ግለሰባዊ፣ ተቋማዊ እና ሀገራዊ ግዴታ መሆኑን የገለጹት አፈ ጉባኤው፣ በተለይም በበዓላት ወቅት አንዱ ለሌላው አጋርነቱን በተግባር በማሳየት አርአያነት ያለው ተግባር ማከናወን እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ለሠራተኞች የሚደረገው ድጋፍ የእጥረት መግለጫ ሳይሆን፣ በማንኛውም ማኅበራዊ መስተጋብር ውስጥ አለኝታነትን ለማሳየት ጭምር እንደሆነም አብራርተዋል።

አክለውም፣ ድጋፍ ለማድረግ የሀብት መትረፍረፍ ብቻ ሳይሆን፣ ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል እንደ አቅሙ ካለው ላይ ቀንሶ መደገፍ እና መተጋገዝ እንደሚጠበቅበት አሳስበዋል።

አቶ አገኘሁ በመጪው አዲስ ዓመት የተሰጡንን ተልዕኮዎች እና የተጣሉብንን ኃላፊነቶች በጋራ በመወጣት፣ ሀገራችንን ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገር መረባረብ እንደሚገባ ጠቁመው፣ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መልካም ምኞች ማስተላለፋቸውን ከምክር ቤቱ ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: