Search

ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች በሁሉም መስክ የወደፊቱ ሀገር መሪዎች የሚፈጠሩባቸው ተቋማት እንዲሆኑ እየተሠራ ነው፦ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

ማክሰኞ መስከረም 05, 2019 127

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ የፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች በሁሉም በኩል የወደፊቱ የሀገር መሪ የሚሆኑ ዜጎች የሚፈልቁባቸው ተቋማት ይሆናሉ ሲሉ አዲስ ከተመደቡ የፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች መምህራን ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት ገለጹ። ትምህርት ቤቶቹ የነገዋን ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ፣ በሳይንስ፣ በፖለቲካ፣በፍልስፍና በሌሎችም የሚገነቡ ሀገር ወዳድ ዜጎች መፍለቂያዎች እንደሚሆኑ ያላቸውን እምነት ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

ለሁሉም እኩል የሚያስቡ እና ሁሉንም እኩል መምራት እና ማገልገል የሚችሉ፤ ሀገርን ከቅርቃር እና ከችግር ማውጣት የሚችሉ ዜጎች የሚፈጠሩባቸው ተቋማት እንደሚሆኑም ጠቅሰዋል።

ትምህርት ቤቶቹ ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች የተውጣጡ ዜጎች የሚማሩባቸው እና ከሁሉም ቦታ የተውጣጡ መምህራን እና በችሎታ ተመርጠው የሚያስተምሩባቸው ተቋማት መሆናቸውንም ጠቁመዋል።

ዓለም በፍጥነት እየተለወጠች መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ፣ ከጥገኝነት የተላቀቀች ሁለተኛ የማትለምን ሀገር መፍጠር እንደሚገባም ጠቁመው  በልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶቹ አዲስ የተመደቡ መምህራን ተገቢው እውቀት በማስተላለፍ እና በሥነ-ምግባር በማነጽ አዲስ ዓይነት ትውልድ የመፍጠር ኃላፊነት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

የትምህርት ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር ክንደያ /ሕይወት በበኩላቸው፣ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች እንደ ሀገር ከነበሩብን ችግሮች የምንወጣባቸው እርሾ ፕሮጀክቶች መሆናቸውን ተናግረዋል።

እነዚህ ልዩ አዳሪ 2 ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለሌሎችም ትምህርት መነሻ (benchmark) በመሆን በሞዴልነት እንደሚያገለግሉም አመላክተው በትምህርት ቤቶቹ የተመደቡ መምህራን ከተለመደው አሠራር ባሻገር ድርብ ኃላፊነት ያለባቸው መሆኑን ጠቅሰዋል።

የመምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች /መሪ ሥራ አስፈጻሚ / አሰገደች ምሬሳ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት፣ አዲሰ የተመደቡ መምህራን ወደየተመደቡባቸው ትምህርት ቤቶች በመሄድ ሥራቸውን መጀመር እንዳለባቸው ማሳሰባቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: