Search

የኢትዮጵያ ወጣቶች በሩሲያ የዓለም ወጣቶች ፌስቲቫል ላይ የሀገራችንን ውብ ባህል እያሳዩ ነው

ረቡዕ መስከረም 06, 2019 65
የኢትዮጵያ ወጣት ልዑካን በሩሲያ እየተካሄደ ባለው የዓለም ወጣቶች ፌስቲቫል ላይ የሀገራቸውን ውብ የባህል ሀብት፣ ታሪካዊ ቅርሶች፣ የቱሪዝም መስህቦች እና ልዩ ሀገራዊ መታወቂያዎችን ለዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ አስተዋውቀዋል።
ወጣቶቹ በዚህ ታላቅ ዓለም አቀፍ መድረክ ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች ከተወጣጡ ወጣቶች ጋር በነበራቸው የጠበቀ ግንኙነት የኢትዮጵያን ጥንታዊ ታሪክ፣ የእንግዳ ተቀባይነት ባህል እና የመስህብ ስፍራዎችን በሚገባ ማስገንዘባቸውን የቱሪዝም ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።
 
 
እንዲሁም ውጤታማ የሕዝብ ለሕዝብ የዲፕሎማሲ ሥራ ማከናወናቸውም ተገልጿል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: