በአማራ፣ በሲዳማ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች፣ እንዲሁም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ሶዶ ከተማ የ2019 ዓ.ም መደበኛ የመማር ማስተማር ሥራ በዛሬው ዕለት በይፋ ተጀምሯል።
በዚህም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አዲስ እና ነባር ተማሪዎች ከክረምት ዕረፍት መልስ ወደ ትምህርት ገበታቸው ተመልሰዋል።
በአማራ ክልል በአጠቃላይ 4.8 ሚሊዮን ተማሪዎች ለዘንድሮው የትምህርት ዘመን የተመዘገቡ ሲሆን በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች የመማር ማስተማር ሂደቱ ጀምሯል።
በሲዳማ ክልል ከቅድመ መደበኛ ጀምሮ እስከ 12ኛ ክፍል የሚገኙ 1.3 ሚሊዮን ተማሪዎች ትምህርታቸውን ጀምረዋል።
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ደግሞ ከ320 ሺህ በላይ ተማሪዎችን በመቀበል በተለያዩ የግል እና የመንግሥት ትምህርት ቤቶች ትምህርት ተጀምሯል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ሶዶ ከተማ፣ በ243 ትምህርት ቤቶች ከ67 ሺህ በላይ ተማሪዎችን በመቀበል ትምህርት ተጀምሯል።
በተለያዩ ትምህርት ቤቶች የተገኙ ተማሪዎች፣ በመጀመሪያው ቀን በትምህርት ገበታ ላይ መገኘታቸው ለዓመቱ ስኬት ስንቅ እንደሚሆናቸው ተናግረዋል።
ተማሪዎች የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ በቂ ዝግጅት አድርገው መምጣታቸውን ገልጸዋል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: