Search

የጋሞ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ በዓል “ዮ ማስቃላ” ድምቀት

ዓርብ መስከረም 08, 2019 49

የጋሞ ዞን ሕዝቦች በጉጉት የሚጠብቁትና በድምቀት የሚያከብሩት የዘመን መለወጫ በዓል ማስቃላከወዲሁ የዝግጅት ሥራዎች ተጀምረዋል። በዓሉ ከማክበርም ባለፈ ማህበራዊ ትስስርን የሚያጠናክር፣ ይቅርባይነትን የሚሰብክና የባህል እሴቶች የሚንጸባረቁበት ትልቅ ኩነት ነው።

ለበዓሉ ገንዘብ የማሰባሰብ ዝግጅት የሚጀምረው ቀደም ብሎ ሲሆን በዚሁ መልኩ ዓመቱን ሙሉ ገንዘብ በመቆጠብ በዓሉን በድምቀት ለማክበር ዝግጅት ይደረጋል።

ወንዶች ለሠንጋ መግዣና ለልጆች ጌጣጌጥ፣ እናቶች ደግሞ ለቅቤ፣ ቅመማቅመም እና ባህላዊ ምግቦች እህል ማግዣ ዓመቱን ሙሉ በንቃት ይቆጥባሉ።

የገብስ ቅንጬ፣ ከቡላና ገብስ የሚዘጋጅ ቂጣ፣ የቡላ ፍርፍር፣ የሐረግ ቦዬ እንዲሁም ቦርዴ እና የማርና ቦርዴ ውህድ በስፋት ይዘጋጃሉ።

በዓሉ ለሰው ልጆች ብቻ ሳይሆን ለእንስሳትና አዕዋፍም ይተርፋል። ምግብ ይትረፈረፋል፤ ለከብቶችም የግጦሽ መሬት በየአካባቢው ይከለላል።

በተለያዩ አጋጣሚዎች ተጣልተው  የነበሩ ሰዎች ታርቀው፣ ዘመድ አዝማድና ወዳጆች ተሰባስበው በጋራ የሚያከብሩት የሰላም በዓል ነው።

መስከረም ወር የመጀመሪያው ቀን በጋሞ ዞንሂንግጫተብሎ የሚጠራ ሲሆን ይህም አዲሱን ዓመት ለመቀበል ዝግጀት የሚደረግበት ቀን ነው። የተለያዩ አገልግሎት የሚሰጡ የገበያ ቀናትም ይገኛሉ።

ጋሜ ጊያየእርድ ከብቶች እና ለማስቃላ በዓል የሚሆኑ ልዩ ልዩ ቁሳቁስ የሚገዛበት ነው፤  “ዩሼ ጊያወላድ እናቶች በማስቃላ በዓል ገበያ ወጥተው ዘና የሚሉበት ነው፤ጎሻ ጊያየማስቃላ ዝግጅት ካበቃ በኋላ የመጨረሻው ገበያ ሆኖ እንደ ቅመማቅመም የመሳሰሉ ጥቃቅን ነገሮች የሚሸምቱበት እና ፈጥነው የሚመለሱበት በመሆኑ እንደወትሮው የደራ ገበያ አይሆንም።

በጋሞ ዞን የማስቃላ የእርድ ሥነ-ሥርዓት ከቦታ ቦታ ይለያያል። እርዱ በየቡድኑ በተደራጁ ቤተ-ዘመዶች ወይም ጎረቤቶች ገበያ ላይ አልያም አማካይ በሆነ ቦታ ይከናወናል።

በባህሉ መሠረት ችቦ የሚወጣበት ሰዓት ሲደርስ አባት የራሱን ችቦ ለኩሶ የቅቤ ምንቸቱን፣ የቤቱን ምሰሶ፣ የከብቶቹን ጋጣ እና የበር ጉበኖችን ግራ እና ቀኝ በችቦው ጫፍ ያነካካል።

በዕለቱ የሚዘጋጀው ባህላዊ ምግብ ገንፎ ሲሆን ይህንን ወንዶች ከጭፈራ ሲመለሱ ተሰባስበው ከአንድ ወጭት ... ማስቃላ እያሉ ሁሉም የቤተሰብ አባላት፣ ዘመድ አዝማድ እና ጎረቤቶች ያለ ልዩነት በጋራ ይመገባሉ። በጋሞ ብሔረሰብ የሚከበረው የማስቃላ በዓል በሶፌ ሥርዓት የታጀበ ነው።

 

የቀደመው ዓመት ማስቃላ በዓል ከተከበረ በኃላ የተጋቡ ሙሽሮች ከመስከረም አጋማሽ ጀምሮ ማምሻውን በአደባባይ ከመላው ህብረተሰብ ጋር የሚቀላቀሉበት እና ሁለቱም ተጋቢ ቤተሰቦች አንድ ላይ ሆነው ደስታቸውን የሚገልፁበት ሥርዓት ነው።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: