የኩርሙክ ጎልድ ማይን ኃ.የተ.የግ.ማ. የሙከራ የወርቅ ምርቱን ለማምረት የሚያስችለውን ዝግጅት አጠናቅቆ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ መድረሱን የማዕድን ሚኒስቴር አስታወቀ።
ሚኒስቴሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ እንዳለው፣ የአላይድ ጎልድ ኮርፖሬሽን አካል የሆነው ኩርሙክ ጎልድ ማይን ኃ.ተ.የግ.ማ. የመጀመሪያ የወርቅ ምርቱን ለማምረት ዝግጁ መሆኑን በይፋ አሳውቋል።
ኩባንያው ከዓመታት የፍለጋ፣ የምህንድስና እና የግንባታ ሥራዎች በኋላ የመጨረሻውን የተግባር ሙከራ (Commissioning) ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።
ኩርሙክ አዲስ የልማትና የምርት ምዕራፍ ውስጥ በመግባት ለሀገራችን ኢኮኖሚ፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራ እና ለዘርፉ ዕድገት አዲስ ተስፋ ይዞ እየመጣ ነው ብሏል የማዕድን ሚኒስቴር።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: