የወላይታ ብሔር የዘመን መለወጫ "ጊፋታ" በዓልን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀው ታላቁ የጊፋታ ሩጫ ዛሬ በወላይታ ሶዶ ከተማ ተካሂዷል። በሩጫ ውድድሩ ላይ በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊ ሆነዋል።
በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ የሚገኘው የዘንድሮው የጊፋታ በዓል፣ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በዓለም የማይዳሰስ ባህላዊ ቅርስነት ከተመዘገበ በኋላ የሚከበር የመጀመሪያው ዓመት በመሆኑ የተለየ ትኩረት ተሰጥቶታል።
በነገው ዕለትም "የወላይታ ቋንቋና ባህል ሲምፖዚየም" በወላይታ ጉታራ አዳራሽ እንደሚካሄድ ታውቋል።
ዓምና በዩኔስኮ የተመዘገበው የጊፋታ በዓል በተለያዩ የዋዜማ ዝግጅቶች በድምቀት እየተከበረ የሚገኝ ሲሆን፣ በመስከረም 10 ቀን 2019 ዓ.ም “የትውልድ ቅርስን እንጠብቅ፣ የጊፋታን ውርስ እናስቀጥል” በሚል መሪ ቃል በአደባባይ በድምቀት ይከበራል።
በትዕግስቱ ቡቼ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: