Search

የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም የሚያስጠብቅ ትውልድ ለመቅረጽ በትምህርት ዘርፍ ሰፊ የሪፎርም ስራዎች እየተከናወኑ ነው፦ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

ዓርብ መስከረም 08, 2019 33

የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም የሚያስጠብቅ፣ ብቁ፣ በቴክኖሎጂ የዳበረ፣ አገር ወዳድ እና ከግል ጥቅም ይልቅ ለጋራ ጥቅም የሚያስብ ትውልድ ለመፍጠር ያለመ የትምህርት ስርዓት አተገባበርን ባለፉት ሦስት ዓመታት ተኩል ውስጥ በትኩረት ስትተገብር ቆይታለች።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከኢቲቪ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ አዳዲስ የስርዓተ-ትምህርት ማሻሻያዎችን ከመተግበር ጀምሮ፣ የብሔራዊ ፈተና አሰጣጥን በማጥበቅ የኩረጃን ልማድ ከመከላከል አንጻር ሰፊ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸዋል።

በዚህም ባለፉት 3 ዓመታት ህብረተሰቡን በማሳተፍ በተሰበሰበ 146 ቢሊዮን ብር ወጪ 17 ሺህ በላይ አዳዲስ ትምህርት ቤቶች መገንባታቸውን የገለጹት ሚኒስትሩ፣ 36 ሺህ በላይ የሚሆኑ ነባር ትምህርት ቤቶችም እድሳት ተደርጎላቸዋል ብለዋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የቅድመ-መደበኛ ትምህርት ቤቶች ቁጥር ከነበረበት 4 ሺህ ወደ 36 ሺህ ከፍ ሊል ችሏል።

ከትምህርት መሣሪያዎችና ከአቅም ግንባታ አንጻርም ከተካሄደው የስርዓተ-ትምህርት ማሻሻያ 45 ሚሊዮን በላይ የሁለተኛ ደረጃ መማሪያ መጻሕፍት ታትመው ለተማሪዎች የተዳረሱ ሲሆን፣ 120 ሺህ እስከ 130 ሺህ የሚጠጉ መምህራንም በዘመናዊ የሥልጠና አሰጣጥ ዘዴዎች አቅማቸውን የሚያሳድግ ስልጠና እንዲያገኙ ተደርጓል።

በየትኛውም የኢትዮጵያ ወረዳ የመማሪያ ተቋም የሌለበት ቦታ እንዳይኖር ለማስቻል የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን፣ በዘንድሮው ዓመት በሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ዲጂታል ቤተ-መጻሕፍት እና ላቦራቶሪዎች እንዲኖሯቸው ይደረጋል ብለዋል።

በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲዎች በከፍተኛ ፍጥነት ባለው የፋይበር ኦፕቲክ ቴክኖሎጂ ተገናኝተው ዓለም አቀፍ የትምህርት መረጃዎችን በነጻ ማግኘት የሚችሉበት ስርዓት በሚቀጥሉት አራት ወራት ውስጥ ይዘረጋል።

የትምህርት ሚኒስቴር ከብሪቲሽ ካውንስል ጋር በመተባበር 7 እና 8 ክፍል ተማሪዎችን የእንግሊዘኛ ቋንቋ ችሎታ ለማሳደግ የሚያስችል 5 ሚሊዮን ፓውንድ ፕሮጀክት መጀመሩንም ግለጸዋል። ይህም ፕሮጀክት መምህራንን በስፋት የማሰልጠን እና የመማሪያ መሳሪያዎችን የማዘጋጀት ስራዎችን ያካተተ ነው።

የብሔራዊ ፈተና አሰጣጥን በማዘመን፣ የኩረጃ ችግርን በመከላከል እና በብሔራዊ ማንነት ላይ የተመሠረተ ትውልድ ለመፍጠር የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አረጋግጠዋል።

 

በላሉ ኢታላ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: