በአፍሪካ ምድር ግዙፍና አከራካሪ ከሆኑት የውሃ መሰረተ-ልማቶች አንዱ የሆነው የግብፅ የአስዋን ከፍተኛ ግድብ ግንባታ፣ የታሪክ ጥቁር ጥላ ያረፈበትና የአንድ ወገን ውሳኔ ውጤት እንደሆነ የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ።
የዚህ ግድብ መገንባት ከመቶ ሺህ በላይ የሚሆኑ የኑቢያ ማህበረሰብ አባላትን ከአባቶቻቸው ርስትና መኖሪያ ቀዬ ያፈናቀለ፣ ህይወታቸውንና ማህበራዊ መሰረታቸውን ለከፍተኛ ውድመት የዳረገ አደጋ ነበር።
ግብፅ የአስዋን ግድብን ስትገነባ የላይኛውን የተፋሰስ ሀገራት በተለይም ኢትዮጵያን ያላማከረችና ያገለለች ሲሆን፣ ኢትዮጵያም በተደጋጋሚ የውይይትና የድርድር ጥሪዎችን ብታቀርብም ግብፅ ግን ያለ ኢትዮጵያ ፈቃድና ስምምነት ፕሮጀክቱን ገፍታበታለች።
ከአውሮፓውያኑ 1952 እስከ 1960 ባሉት ዓመታት የተመዘገቡ ከ15 በላይ ይፋዊ የአሜሪካ እና የብሪታንያ ሰነዶች እንደሚያስረዱት፣ በወቅቱ ኢትዮጵያ በአስዋን ግድብ ግንባታና ቀደም ሲል በነበሩት የዓባይ ውሃ ስምምነቶች ላይ የምክክር ማነስን በመቃወም ያቀረበችውን ይፋዊ ተቃውሞና የተፋሰሱን ሀገራት አለማማከር ያስከተለውን ውጥረት በግልጽ ያሳያሉ።
በአንፃሩ ኢትዮጵያ የገነባችው የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ (GERD) በአውሮፓውያኑ 2015 በኢትዮጵያ፣ በግብፅ እና በሱዳን መካከል በተፈረመው የመርሆዎች ስምምነት (DoP 2015) ዘመናዊ የህግ ማዕቀፍን ተከትሎ የተከናወነ ህጋዊና ፍትሃዊ ፕሮጀክት ነው።
በመሆኑም በ1950ዎቹ ኢትዮጵያ ያቀረበችውን ህጋዊ ተቃውሞ ወደ ጎን ብላ፣ መቶ ሺህ የኑቢያ ህዝቦችን አፈናቅላ ያለ ምንም ምክክር ግድብ የገነባችው ግብፅ፤ ዛሬ ላይ ኢትዮጵያ የታችኞቹን የተፋሰስ ሀገራት አላማከረችም በሚል የምታቀርበው ወቀሳ ፍፁም የሞራል መሰረት የሌለውና የዘመናት ሴራዋ ማሳያ ነው።
ግብፅ በታሪክ ያከናወነችው ይህ እኩይ አሰራር ዛሬ ላይ ኢትዮጵያን ለመክሰስ የሚያስችላትን ማንኛውንም የሞራል ልዕልና ያሳጣታል።
#ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ #ታላቅ_ርዕይ ሰንቃ የተነሳችው ኢትዮጵያ፣ የካይሮን የደባና የፕሮፓጋንዳ ስልት በመበጣጠስ፣ የራሷን የውሃ ሀብት በፍትሃዊነትና በህጋዊ መንገድ በመጠቀም የመልማትና የመበልጸግ አቅሟን በተግባር ማረጋገጧን ትቀጥላለች።
በጌቱ ላቀው
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: