Search

ኢትዮጵያና ስሎቫኪያ በሰላማዊ የኒውክሌር ኃይል ልማት ትብብር ዙሪያ ተወያዩ

ሰኞ ኅዳር 14, 2019 36

የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን ኮሚሽነር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የስሎቫኪያ አምባሳደር ከሆኑት ራስቲስላቭ ክሪዣን እና ከምክትል አምባሳደር ኢንግሪድ ሩዚችኮቫ ጋር በኮሚሽኑ ዋና መሥሪያ ቤት የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል።

ኮሚሽነር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) በውይይቱ ወቅት ኢትዮጵያ እያስመዘገበች ያለውን ፈጣን የኢንዱስትሪና የኢኮኖሚ ዕድገት ለመደገፍ የኃይል ምንጮቿን ማስፋፋትና የኒውክሌር ኃይልን በሀገሪቱ የኃይል ሥርዓት ውስጥ ማካተት ያለውን ስትራቴጂያዊ ፋይዳ አብራርተዋል።

አምባሳደር ራስቲስላቭ ክሪዣን በበኩላቸው ስሎቫኪያ በኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ቴክኖሎጂ፣ በኒውክሌር ደኅንነት አጠባበቅና በዘርፉ የረጅም ጊዜ አስተዳደር ያካበተችውን ልምድ አንስተዋል።

ሁለቱ ወገኖች በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በሰው ኃይል አቅም ግንባታና ሥልጠና፣ እንዲሁም በኒውክሌር መሠረተ ልማት በጋራ ሊሠሩባቸው በሚችሉ ጉዳዮች ላይ መክረው፣ የሁለትዮሽ ትብብራቸውን ለማጠናከር መግባባት ላይ ደርሰዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: