Search

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ምላሽ እና ማብራሪያ ይሰጣሉ

ማክሰኞ ኅዳር 15, 2019 21

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 7ኛ የምርጫ ዘመን፣ 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን ኅዳር 17 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ያካሂዳል፡፡

በመደበኛ ጉባኤውም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፕሬዝዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮች እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ መክፈቻ ስብሰባ ያቀረቡትን የ2019 ዓ.ም የመንግሥት ዕቅድ መነሻ በማድረግ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ምላሽ እና ማብራሪያ ይሰጣሉ፡፡

ይህንንም ተከትሎ ምክር ቤቱ የመንግሥትን አቋም በማዳመጥ የድጋፍ ሞሽኑን ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በዕለቱ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ታዋቂ ሰዎች፣ የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው ሌሎች እንግዶች በክብር እንግድነት ይታደማሉ፡፡

ጉባኤው በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች በቀጥታ ስርጭት የሚተላለፍ መሆኑን ምክር ቤቱ አስታውቋል፡፡

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: